banner

የባንክ ሰራተኛን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ እየታደነ ነው።

#FastMereja I ​በሰንዳፋ በኬ ከተማ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም አንዲት የባንክ ሰራተኛ ላይ ዘግናኝ የነፍስ ግድያ መፈጸሙን ፖሊስ አስታወቀ። ሟች አዳነች ኩምሳ ትባላለች፤ በአላልቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰራተኛና የሰንዳፋ በኬ ነዋሪ ነበረች።

​የክስተቱ ዝርዝር
#​ግድያው፦ ሟች እና ተጠርጣሪው አቶ ፀጋዬ አሳሊፎ የፍቅር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን፣ በዕለቱ ምሽት በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ ተጣልተው ሟች ጥላ በመውጣቷ ግድያው ተከስቷል።

#​አፈጻጸሙ፦ ተጠርጣሪው በመኪና ተከታትሎ መኪናው ውስጥ ካስገባት በኋላ “ጎማጣ” ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሽጉጥ ገድሏታል።

​አሰቃቂ ሁኔታ፦ ተጠርጣሪው ሬሳውን ጥሎ በመጥፋቱ፣ የአዳነች አስከሬን በዱር አራዊት ተበልቶ መገኘቱን የሰንዳፋ በኬ ፖሊስ የምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ንጋቱ አለሙ ለቢቢሲ ገልጿል ገልጸዋል።

​የፖሊስ ምርመራ
​ተጠርጣሪው ወንጀሉን የፈጸመበትን መኪና እና ሽጉጥ በአላልቱ ከተማ ጥሎ መሰወሩ ታውቋል። ፖሊስ በመኪናው ውስጥ የደም ዱካ እና ሽጉጡን እንደ ማስረጃ ያገኘ ሲሆን፣ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

​የሟች አስከሬን ለምርመራ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከተላከ በኋላ በቤተሰቦቿ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ተፈጽሟል።

3 comments

ፍቅር ያሸንፋል December 18, 2025 - 8:28 am

😭😭

Reply
Rahel Agunachew December 18, 2025 - 8:29 am

በ ኢየሱስ ስም 😭😭😭😭😭

Reply
Yordi Mani December 18, 2025 - 8:29 am

RIP

Reply

Leave a Comment