0
#FastMereja I «የአሲምባ ፍቅር» በተሰኘው ቀዳሚ መጽሐፋቸው በአንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትንና ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻሉት ደራሲ ካህሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል ማንጁስ)፣ ሁለተኛ ስራቸው የሆነውን «ያልተመለሱ ዳናዎች» የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ለንባብ አብቅተዋል።
የመጽሐፍ ምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን፣ በዕለቱም ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ ደራሲያን፣ የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች እና የደራሲው ወዳጅ ዘመዶች ታድመዋል።
“ያልተመለሱ ዳናዎች” 332 ገፅ ያለው ሲሆን በ600 ብር ለገበያ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሰራዊት ትዝታ እና ኩርባዎችን የሚተርክ መፅሐፍ መሆኑ ተገልጿል።
#ኹነት




