#FastMereja I ባራቶን ኤንኤፍሲ ሶሉሽንስ (Baraton NFC Solutions) ከኩባዲስ ሶሉሽንስ ጋር በመተባበር የወረቀት ቢዝነስ ካርድን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚተካ አዲስ የNFC ምርት ዛሬ ታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም በማሪዮት ኤክስኪውቲቭ ሆቴል በይፋ አስመረቀ።
ይህንን ፈጠራ ወደ ሀገር ውስጥ በማምጣትና በማልማት ረገድ ቀዳሚውን ሚና የተጫወተው የ13 ዓመቱ ታዳጊና የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ነው። ታዳጊው አባቱ ለስራ ጉዞ በርካታ የወረቀት ካርዶችን ሲይዙ በመታዘቡ “ይህንን ብክነት በቴክኖሎጂ እንዴት ማስቀረት ይቻላል?” በሚል ባደረገው ጥናት ቴክኖሎጂውን ለሀገር በቀል አገልግሎት እንዲውል አድርጓል።
ካርዱን ወደ ስልክ “Tap” በማድረግ ብቻ የግለሰብን ወይም የድርጅትን መረጃ (ፖርትፎሊዮና ቪዲዮን ጨምሮ) በቀጥታ ወደ ስልክ ያስተላልፋል።
ለአንዴ ታትሞ ለህይወት ዘመን የሚያገለግል በመሆኑ፣ ተቋማት ለካርድ ህትመት የሚያወጡትን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያስቀራል።
የወረቀት ብክነትን የሚያስቀርና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) ነው።
በምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የሰንሳይሽን ኮንስትራክሽን ባለቤት የሆኑት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ የብራንድ አምባሳደር የሆኑ ሲሆን ፕሮግራሙ ላይ የንግድ መሪዎች፣ የድርጅት ስራ አስኪያጆችና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የታደሙ ሲሆን፣ ባራቶን ኤንኤፍሲ ሶሉሽንስ በ2026 ምርቱን በስፋት ለገበያ በማሰራጨት የኢትዮጵያን የዲጂታል ትስስር ለማዘመን አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።




