0
#FastMereja I በድንገት ህይወቷ ያለፈው ታዋቂዋ ሞዴል ቀነኒ አዱኛ የሞት ሁኔታ፣ በማህበራዊ ሚዲያ እና በቤተሰቦቿ ዘንድ ዳግም እንዲመረመር የሚጠይቁ ድምጾች በመበርከታቸው ጉዳዩ አገርሽቷል።
በዚህ አነጋጋሪ ጉዳይ ዙሪያ የወጡ ዜናዎች የቀነኒ ቤተሰቦች የልጃቸውን ሞት አስመልክቶ ቀደም ሲል “ራስን ማጥፋት ነው” በሚል የተሰጠውን ድምዳሜ እንደማይቀበሉ በመግለጽ፣ ገለልተኛ እና ጥልቀት ያለው ምርመራ እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ እያቀረቡ ነው።
በተለይም በቲክቶክ እና በፌስቡክ ላይ ስለ ሞዴሏ ህይወት እና ስለ ሞቷ ምስጢራዊነት የሚተነትኑ ቪዲዮዎች በስፋት መሰራጨታቸው፣ ጉዳዩ የብዙዎችን ትኩረት እንዲስብ አድርጓል።
ጉዳዩ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እና የፍትህ መዘግየትን በተመለከተ ሰፊ ውይይት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል።
የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት በወቅቱ ከህንጻ ላይ ወድቃ እንደሆነ ቢነገርም፣ እስካሁን ድረስ በቤተሰቦቿ እና በአድናቂዎቿ ዘንድ አሳማኝ ምላሽ ያላገኘ እንቆቅልሽ ሆኖ ቀጥሏል።

2 comments
Menw falegat edee
እመን ትድናለህ አንዱ