banner

የሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጎበኙ!

#FastMereja : የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በከፍተኛ ወጪ ወደ ሀገር ባስገባቸው ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች ዘረመል መለየትን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ ምርመራዎችን እያከናወነ መሆኑን በዛሬዉ እለት ከሚዲያ አካላት ጋር በተካሄደዉ ፎረም ተገልጿል።

እንዲሁም በአሁን ሰአት በሀገራችን ተላላፊ በሽታዎች መብዛቱን ተከትሎ ከ75 % በላይ የሆኑ ተላላፊ በሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ መሆናቸውንና ኢንስቲትዩቱም ይህን የተላላፊ በሽታዎች መከላከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል::

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እንደገለፁት ለ100 ዓመታት ሕብረተሰቡን ሲያገለግል የቆየው ኢንስቲትዩቱ፤ ራሱን በዘመናዊ ላብራቶሪ እና ቴክኖሌጂዎች በማደራጀት የበሽታን መነሻ ማወቅ የሚያስችሉ እና የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

በተጨማሪም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ወይም ወረርሽኝ በሚከሰትበት ወቅት የዳሰሳ ጥናት እና ምርምር በማድረግ ኢንስቲትዩቱ ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ እና ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ተላላፊ በሽታዎች ላይ ተገቢውን የቁጥጥር ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

በዛሬዉ እለት ከተካሄደዉ ፎረም በተጨማሪ የህዝብ ጤና ድንገተኛ አስተዳደር ማእከል እና የብሔራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ጉብኝት አካሂዷል።





Leave a Comment