0
#FastMereja I የአልቲማ ሪል እስቴት ብራንድ አምባሳደር የሆነው ተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ተከትሎ ተቋሙ መራር ኀዘን እንደተሰማው ገለጸ።
አልቲማ ሪል እስቴት ባወጣው መግለጫ፣ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ የተቋሙ Brand Ambassador ከመሆኑ ባለፈ፣ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚያቀርበው “የቤተሰብ ጨዋታ” ፕሮግራም፣ በተሳተፈባቸው ፊልሞችና በሚያደርጋቸው ማስታወቂያዎች በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበረ የጥበብ ሰው መሆኑን አውስተዋል።
ተቋሙ የአርቲስቱን ድንገተኛ መለየት አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፦
”ተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ድርጅታችን አልቲማ ሪል እስቴት ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶታል። ነጻነት በሥራው ካሳየው ብቃት ባሻገር ለድርጅታችን ዕድገትና ስኬት የነበረው አስተዋጽኦ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።”
አርቲስቱ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት እንደነበረ የገለጸው አልቲማ ሪል እስቴት፣ ለባለቤቱ፣ ለልጆቹ፣ ለቅርብ ወዳጆቹና ለናፋቂ አድናቂዎቹ በሙሉ “ፈጣሪ መጽናናትን ይስጣችሁ” በማለት ገልጿል።
