#FastMereja I የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በአጋርነት የሰራው በሎተሪ ታሪክ በሽልማት መጠኑ ከፍተኛ የሆነው የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የዕድል አዳራሽ በሕዝብ ፊት በይፋ ወጥቷል ።
📌 የአንደኛ ዕጣ (60 ሚሊዮን ብር) የእጣ ቁጥር 6361547 ሆኖ ወቷል።
ባለ እድሉ ከባሌ ጎባ ሲሆን በሻይ ቡና ስራ የሚተዳደር ነዉ።
📌 የሁለተኛ ዕጣ (20 ሚሊዮን ብር) የእጣ ቁጥር 5681025 ሆኖ ወቷል።
ባለ እድሉ አቶ ማስረሻ ሲሆኑ የኮልፌ ቀራንዮ ነዋሪ ሲሆን በታክሲ ሾፌር የሚተዳደር ነዉ።
📌 የሦስተኛ ዕጣ (10 ሚሊዮን ብር) የእጣ ቁጥር 7699884 ሆኖ ወቷል።
ባለ እድሉ ብዙነህ አዲስ ሲሆን የቢሾፍቱ ነዋሪ ሲሆን በግል ስራ የሚተዳደር ነዉ።
የዛሬውን እጣ ልዩ የሚያደርገው በሀገራችን ታሪክ ከፍተኛው የሽልማት መጠን መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪው ለመጀመሪያ ጊዜ ለደንበኞች በዲጂታል መንገድ ብቻ ለሽያጭ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የወረቀት ሎተሪዎችን በዲጂታል የማዘመን ሥራ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ አንዱ አካል ነው። ተቋሙ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ይህን ታሪካዊ ሎተሪ በዲጂታል ብቻ ለገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል።
በመጨረሻም፣ ይህ የታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን የዲጂታል ሎተሪ ስኬታማ እንዲሆን በአጋርነት አብረው ለሠሩት ለኢትዮ ቴሌኮም (ቴሌብር)፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለአዋሽ ባንክ፣ ለኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ ለዳሽን ባንክ፣ ለአቢሲኒያ ባንክ፤ ለዘርጋው ክላውድ አገልግሎት፣ ለኤዲሲ ሪሰርችና ዲቨሎፕመንት እንዲሁም ለሌሎች አጋሮች ምስጋና አቅርቧል።





6 comments
እንኳን ደስ አለህ!
ሁሌ የአዲስአበባ ሰው ከእጣ አይጠፋም
ውሸት በጣም ውሸት ነወ
ለአንድ ሰው እንደሚወጣለት እርግተኛ ነበርኩ
እንኳን
ቀሪዎቹ ዕጣዎችስ?