banner

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ያስገነባዉን ህንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ በአዳማ ከተማ አስመረቀ!

#FastMereja I የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ያስገነባዉን ህንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዳማ ከተማ በዛሬዉ እለት አስመርቋል።

ይህ ማዕከል አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አስተማማኝና ተደራሽ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ ባለ 5 ወለል ህንፃና የፍተሻ ላቦራቶሪዎችን አካቶ እንደተገነባ ተገልጿል።

በዛሬዉ እለት የተመረቀዉን ህንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከ140 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት እና ዘጠነኛ ቅርንጫፍ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት እና የአገልግልሎት ጥራትን ለማስጠበቅ የፍተሻ፣ የሰርተፍኬሽን እና የኢንስፔክሽን አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ እንደተገነባ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አጠቃላይ በክልል ከተሞች 9 ቅርንጫፎች እንዳሉት የተገለፀ ሲሆን በጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳ፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ መቀሌ፣ እና አዳማ ተጠቃሽ ናቸው ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡





Leave a Comment