banner

የነቢይ ኢዩ ጩፋ መፅሀፍ ለንባብ ሊበቃ ነዉ!

#FastMereja -የክራይስት አርሚ ቤተክርስትያን እና ቲቪ መስራች የነብይ ኢዩ ጩፉ ገናናዉ እየሱስ የተሰኘዉ መፅሀፍ ለንባብ ሊበቃ መሆኑን በዛሬዉ እለት በተሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ይህ መፅሀፍ ከጥልቅ መንፈስ እና ፀሎት እንደተፃፈ ገልፆ ሰዎች ይህን መፅሀፍ ካነበቡ በኋላ ቅዱሳን ለወንጌል እንዲነሳሱ የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ መፅሀፍ እሁድ የካቲት 1/2018 ዓ.ም ከሁለት ሰአት ጀምሮ በክራይስት አርሚ ቤተክርስትያን እንደሚመረቅ ተገልጿል።

ይህ መፅሀፍ ከህፃን እስከ አዋቂ አንብበዉ መረዳት እንዲችሉ ተደርጎ እንደተፃፈም ነቢይ ኢዩ ጩፋ ተናግሯል።

በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው፣ መጽሐፉ በመጀመሪያው ዕትም 5ዐ ሺህ ኮፒዎች ታትሞ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ክራይስት አርሚ ቤተክርስትያን ከተመሰረተ 13 አመታት እንዳስቆጠረ እና በ13 አመታት ምዕመናንን በስነ ልቦና እና በመንፈሳዊ ህይወት የብዙዎችን ህይወት የቀየረ እንደሆነም ተነግሯል።

ይህ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባን ጨምሮ 3 አጥቢያ ሲኖሩት ከአስር ሺህ በላይ አባላት እና ከመቶ ዘጠና አራት በላይ ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉትም ነዉ የተገለፀዉ።





4 comments

Kükùshä Mïshö Tsëgāyë January 26, 2026 - 3:41 pm

ልክ ነው የእግዚአብሔር ሰው

Reply
Ibsa Niguse Bekele January 26, 2026 - 3:41 pm

Wawu Best

Reply
Cctv Et Habtamu January 26, 2026 - 3:42 pm

ሳስበው የማረሻል አርት መጵሀፍ ነው

Reply
Yomi Yama January 26, 2026 - 3:42 pm

ዘይቷ ትሻለው ነበር እዩ ካራትስቱ

Reply

Leave a Comment