#FastMereja :- ፊንቴክስ FINTEX ኢትዮጵያ ኤክስፖ የፈርኒቸር፣ የቤተ-ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ቴክኖሎጂዎች ዓለም አቀፍ አውደ-ርዕይ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ይፋ ተከፍቷል።
ይህ አዉደ-ርዕይ ከጥር 19 – ጥር 22 ቀን 2018 ዓ/ም እንደሚቆይም ነዉ የተገለፀዉ።
በአውደ – ርዕይው ላይ ከ4ዐዐዐ የሚበልጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት ከስመጥር የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስር እንደሚያድርጉ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
ፊንቴክስ አውድ-ርዕይ ላይ የአገር ውስጥ አምራቾችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰባሰብ ከመላ አገራችን ከሚመጡ ከመንግስት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከዲፕሎማቲከ ማህበረሰብ እና ከበጎ አድራጎት ተቋማት፣ በመገንባት ላይ ከሚገኙ ባንኮች፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንግድ ማዕከላት፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ ከአነስተኛና ጥቃቅን በማደግ ላይ ለሚገኙ የፈርኒቸር አምራቾች እንዲሁም ወኪል ሆነው በክልል ከተሞች ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በፈርኒቸር፣ በቤተ-ውበት እና በግንባታ አጨራረስ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የሚተጉ ግዙፍ የአገር ውስጥ አምራቾች ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል መድረከ እንደሆነ ተነግሯል።
ኤክስፖው በሀገራችን በልዩነት በተመረጡ ዘርፎች ላይዓውደ-ርዕይ በማዘጋጀት በሚታወቁት ፕራና ኤቨንትስ እና አፍሪካን ትረስትድ ፓርትነርስ በጋራ መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡




