banner

በመኪና ውስጥ የወሲብ ድርጊት መፈጸም በሕግ እንደሚያስቀጣ ተገለጸ

​#FastMereja I በተለያዩ አጋጣሚዎች በመንገድ ላይ በሚቆሙ መኪናዎች ውስጥ የሚፈጸሙ የወሲብ ድርጊቶች “ለመልካም ሥነ-ምግባር እና ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ” በመሆናቸው በሕግ እንደሚያስቀጡ የሕግ ባለሙያ ማብራሪያ ሰጡ።

​ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፣ ድርጊቱ በሕዝብ መሳለጫ ወይም ሰዎች ሊያዩት በሚችሉባቸው የሕዝብ ቦታዎች (Public Places) መፈጸሙ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል አስታውቀዋል።

​እንደ ጠበቃዋ ገለጻ፣ ድርጊቱ በተፈጸመበት ሁኔታና ቦታ ላይ ተመስርቶ ቅጣቱ ሊለያይ ይችላል፦
​በሕዝብ ቦታ ከተፈጸመ፦ ሰዎች ሊያዩት በሚችሉበት ሁኔታ በሕዝብ ቦታ ወይም በመንገድ ዳር መኪና ውስጥ የወሲብ ድርጊት ሲፈጸም ተገኝቶ ጥፋተኛ የተባለ ሰው፣ እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስራት እና በገንዘብ ሊቀጣ ይችላል።

​ሕፃናት በሚያዩበት ሁኔታ ከተፈጸመ፦ ድርጊቱ ይበልጥ ከባድ የሚሆነው ሕፃናት ባሉበት ወይም ሕፃናት ድርጊቱን እንዲያዩ በሚያደርግ ሁኔታ ሲፈጸም ነው። በዚህ ጊዜ የሕግ ምርመራ ተከፍቶ ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ተመልክቷል

​እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ከግል ነፃነት ባለፈ የሕዝብን ሞራልና ማኅበራዊ እሴቶችን የሚነኩ በመሆናቸው፣ ግለሰቦች ከእንዲህ ዓይነት ሕገ-ወጥ ተግባራት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። መኪና ውስጥ የሚፈጸሙ መሰል ድርጊቶች ለወንጀል ምርመራና ለከባድ እስራት ሊዳርጉ እንደሚችሉ ማወቅ ተገቢ መሆኑንም ባለሙያዋ ጨምረው ገልጸዋል።

Leave a Comment