banner

ድሬ ማይክሮፋይናንስ በአዲስ አበባ በቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፉን አስመረቀ!

#Fastmereja: ድሬ ማይክሮፋይናንስ የብድር እና ቁጠባ ተቋም በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ በቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፉን በይፋ አስመርቋል።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማና በገጠር ፤ በሐረር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐረር ከተማ ፣ጅግጅጋ እና ሐሮማያ ከተሞች ቅርንጫፎችን በመክፈት ውጤታማ ሥራ እየሰራ ሲሆን ፤ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ተደራሽነቱን እና አገልግሎቱን ለማስፋት በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ቅርንጫፉን አስመርቋል።

ድሬ ማይክሮ ፈይናንስ ተቋም የሚሰጣቸው የብድር እና የቁጠባ አማራጮች የመደበኛ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት፣የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ (Machinery Lease) የወለድ አልባ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት እና ዲጅታል የቁጠባና ብድር አገልግሎቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

ተቋሙ ራዕይዉን ተከትሎ በትጋትና በቁርጠኝነት በሰራቸው ስራዎች አሁን ላይ የብድር ደንበኞች ላይ ያለው ጠቅላላ የብድር መጠን (Total Loan Outstanding) ከ1.7 ቢሊየን ብር በላይ ማድረስ መቻሉን ገልጿል፡፡

ከ111ሺ በላይ የብድርና ቁጠባ ደንበኞችን ማፍራት የቻለዉ ይህ ተቋም እስከ ዲሴምበር 31/2025 ላለመመለስ በአደጋ ላይ ያለውን ብድር/PAR/ ዐ.73% ማድረስ የቻለ ሲሆን የተቋሙን ካፒታል ከ677 ሚሊየን ብር በላይ ማድረስም ተችሏል፡፡





Leave a Comment