banner

በኢትዮጵያ የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአይፎን በከፍተኛ መጠን ብልጫ እንዳለው ተገለጸ

#FastMereja I ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ይፋ ባደረገው የ”መሣሪያዎች ስርጭት” (Device Penetration) ዳታ መሠረት፣ በሀገሪቱ ካሉ ዘመናዊ ስልኮች (Smartphones) መካከል የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በከፍተኛ ደረጃ የበላይነቱን ይዟል።

በአጠቃላይ 90 ሚሊዮን የተገናኙ መሣሪያዎች ባሉበት በዚህ ሪፖርት፣ የስልኮቹ የገበያ ድርሻ እንደሚከተለው ቀርቧል፡
• አንድሮይድ (Android): በአጠቃላይ በስማርት ስልኮች ገበያ ውስጥ 96.3% የሚሆነውን ድርሻ በመያዝ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል። ይህ ማለት በሀገሪቱ ካሉ 100 ስማርት ስልኮች ውስጥ 96ቱ የአንድሮይድ ስልኮች ናቸው።
• አይፎን (iOS): የአፕል ምርት የሆነው አይፎን የ2.3% የገበያ ድርሻ ብቻ እንዳለው ተመልክቷል።

በሀገሪቱ ካሉ ጠቅላላ መሣሪያዎች ውስጥ 42.2% የሚሆኑት ስማርት ስልኮች ናቸው። ከስማርት ስልኮች በተጨማሪ ፊውቸር ፎኖች (29.1%) እና ቤዚክ ፎኖች (26.6%) አሁንም ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። 29.7 ሚሊዮን የሚሆኑ መሣሪያዎች የ4G (LTE) የኢንተርኔት አገልግሎትን የመደገፍ አቅም አላቸው።

ይህ መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ የዲጂታል ገበያ ውስጥ የአንድሮይድ ስልኮች ተደራሽነት እጅግ ሰፊ ሲሆን፣ የአይፎን ተጠቃሚዎች ቁጥር ግን አሁንም በጣም አነስተኛ መሆኑን ያረጋግጣል።

Leave a Comment