banner

አንጀሊና ጆሊ አሜሪካን ልትሰናበት ነው? የ24.5 ሚሊዮን ዶላር መኖሪያ ቤቷ ለሽያጭ መዘጋጀቱ ተሰማ

#FastMereja I ​ታዋቂዋ የሆሊውድ ኮከብ አንጀሊና ጆሊ ከሎስ አንጀለስ (LA) ወጥታ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ለመጀመር በመዘጋጀት ላይ መሆኗን አዳዲስ መረጃዎች ጠቆሙ። ተዋናይቷ በሎስ ፌሊዝ የሚገኘውና 24.5 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው ታሪካዊ መኖሪያ ቤቷ ለሽያጭ መዘጋጀቱን የሚያሳዩ ምስሎች ይፋ ሆነዋል።

ዴይሊ ሜይል ይፋ ያደረጋቸው ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ ቀደም ሲል ስድስቱ ልጆቿ ሲቦርቁበት የነበረውና የልጆች መጫወቻዎች ሞልተውት የነበረው ግቢ፣ አሁን ላይ እጅግ ተስተካክሎና ለሽያጭ በሚስብ መልኩ ተዘጋጅቶ ይታያል። ቀደም ሲል በግቢው ውስጥ ይታይ የነበረው ግዙፍ የህፃናት መዝለያ (Trampoline) የተነሳ ሲሆን፣ የአትክልት ስፍራውም በልዩ ሁኔታ ተውቦ ለገዢዎች ዝግጁ ሆኗል።

​የአንጀሊና ታናሽ ልጆች ቪቪያን እና ኖክስ በዚህ ዓመት 18 ዓመት ይሞላቸዋል። ይህም ልጆቿ ለአካለ መጠን ስለሚደርሱ በአሜሪካ እንድትቆይ የሚያስገድዳት የቤተሰብ ሁኔታ እንዲቀየር ያደርገዋል።

​አንጀሊና ቀደም ሲል ከቀድሞ ባለቤቷ ብራድ ፒት ጋር በነበራቸው የልጆች አስተዳደግ ክርክር ምክንያት ከሎስ አንጀለስ መውጣት እንዳትችል ተገዳ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ግን ልጆቹ እያደጉ በመምጣታቸው ነፃነቷን እያገኘች መሆኑ ይነገራል።

ተዋናይቷ ባለፈው በጋ ከ1997 ጀምሮ የነበራትን የኒውዮርክ አፓርታማ መሸጧ፣ ከአሜሪካ ለመውጣት ለምታደርገው ዝግጅት እንደ ትልቅ ማሳያ ተወስዷል።

​አንጀሊና ጆሊ ቀደም ሲል በሰጠችው ቃለ መጠይቅ ሆሊውድ “ጤናማ ስፍራ አይደለም” በማለት ወደ ውጭ ሀገር (ምናልባትም ወደ ካምቦዲያ) የመሄድ ፍላጎት እንዳላት መግለጿ ይታወሳል።

Leave a Comment