banner

በእናቶች ጤና ዘገባ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!

#Fastmereja I የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ (SPHMMC) ከቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የማህፀን እና ፅንስ ትምህርት ክፍል(SPIRHR )ጋር በመተባበር በዛሬዉ እለት ከግል፣ ከመንግስት እና ከኦንላይን የሚዲያ ተቋማት ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በእናቶች ጤና ዘገባ ላይ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናዉ በእናቶች ጤና ፣እርግዝና፣ ልጅ መውለድ እና ከወሊድ በኋላ እንክብካቤን እንዲሁም የእናቶች ሞት ዋና ዋና ምክንያቶችን እንዲሁም የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ እና የክህሎት የወሊድ አገልግሎቶች ዙሪያ በዘርፉ ባለሙያዎች ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።

እናቶች በጤና ተቋም ተገቢውን የቅድመ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ለማስቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መስራት እንደሚገባም ተገልጿል።

እንዲሁም በወሊድ ወቅት የደም መፍሰስ የሚያስከትለውን ሞት ለመቀነስም ከደም ባንኮች ጋር በቅርበት በመስራት በወሊድ ወቅት የሚከሰተዉን ሞት መቀነስ እንደሚቻልም ተጠቁሟል።

እናቶች በጤና ተቋማት ስለሚሰጡ አገልግሎቶች የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና የአገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን የራሳቸውን ጤና እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በመድረኩ በጤና ተቋማት ስለሚሰጡ አገልግሎቶችና የእናቶች ቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ አስፈለጊነት ዙሪያ በባለድርሻ አካላት ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በተሰጠው ማብራሪያ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።





Leave a Comment