banner

ለመስኖ አገልግሎት የሚውል ትራንስፎርመር ተሰረቀ፤ አገልግሎቱም ተቋርጧል

#FastMereja I ​በአዳማ ሪጅን አርሲ ዞን ጄጁ ወረዳ በሚገኘው “ተስፋ ሕይወት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለመስኖ አገልግሎት ይውል የነበረ ትራንስፎርመር በዘራፊዎች መወሰዱ ተገለጸ።

​የአዳማ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ጣሃ አህመድ እንደገለጹት፣ ስርቆቱ የተፈጸመው ትላንት የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 5 ሰዓት አካባቢ ነው። የተሰረቀው ትራንስፎርመር 200 ኪ.ቮ.አ/15 ኪ.ቮ.አ አቅም ያለው ሲሆን፣ በወቅቱ ለመስኖ ስራ ይውል የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል።

​እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ይህ አይነቱ በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆት የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ክፉኛ እየጎዳ ይገኛል። በተለይም አርሶ አደሩ በመስኖ በመታገዝ ለሚያከናውነው የምርት ተግባር ትልቅ እንቅፋት ሆኗል።

​በአሁኑ ወቅት፦
​ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል የአካባቢው ነዋሪዎች እና የፀጥታ አካላት በጋራ ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።
​ድርጊቱ በሕግ የሚያስቀጣ በመሆኑ፣ ሕብረተሰቡ መሰል የጥፋት ተግባራትን ሲመለከት በፍጥነት ለሕግ አስከባሪ አካላት እንዲያሳውቅ ጥሪ ቀርቧል።

​የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሰረተ-ልማቶችን መጠበቅ የሁሉንም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን አሳስቧል።

Leave a Comment