banner

ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

#FastMereja I የቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለመጀመር አዲስ አበባ ገብተዋል። ለፕሬዝዳንቱና ለልዑካን ቡድናቸው በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ይህ የፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጉብኝት በሁለቱ ጥንታዊ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው። በቆይታቸውም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Comment