banner

ሆራይዘን የቁጠባና ብድር ተቋም ስራ ጀመረ!

#Fastmereja I ሆራይዘን የቁጠባና ብድር ተቋም በማህበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደዱና ”አይፈቱም” ተብለው የሚታሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በፋይናንስ ድጋፍ ለመፍታት በይፋ ተከፍቶ ስራ ጀምሯል።

ተቋሙ በተለይ የገንዘብ እጥረት ለሚያጋጥማቸው ፈጣሪዎች እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የጀርባ አጥንት ለመሆን አልሞ የተነሳ የፋይናንስ ተቋም እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ፡፡

ይህ ተቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የፋይናንስ ስርአት በመዘርጋት፣ በማህበረሰቡ ዘንድ ተመራጭ እና ታማኝ የፋይናንስ አጋር የመሆን እቅድ እንዳለዉም ነዉ የተገለፀዉ።

ተቋሙ የሚሰጣቸዉ የብድር አይነቶች የስራ ፈጠራ (Startup) ብድር፣የንግድ ማስፋፊያ ብድር፣የሴቶች ተጠቃሚነት ብድር፦ የአጭር ጊዜ የፍጆታ ብድር እንዲሁም የተለያዩ የብድር አይነቶችን እንደሚሰጥ ተገልጿል።

እንዲሁም ሆራይዘን ቁጠባና ብድር ተቋም እና አብሪ ሞተርስ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራርመዋል።

የሆራይዘን ቁጠባ እና የብድር ህብረት ስራ ማህበር – ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ኮር የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያው SACCO በኢትዮጵያ ሲሆን፡፡

አብሪ ጄኔራል ግሩፕ – የነዳጅ መኪና ባለቤቶች በቀላሉ እንዲሸጡ እና ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲሸጋገሩ የሚያስችል ራሱን የቻለ የመኪና ኢ-ኮሜርስ መድረክ የጀመረ የመጀመሪያው የመኪና አስመጪ ነዉ።

ሆራይዘን በ2018 ዓ.ም ስራውን ሲጀምር በአዲስ አበባና በአካባቢው ቢሆንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎቹን በመክፈት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የኑሮ ዘይቤ የመቀየር ራዕይ አለው፡፡





Leave a Comment