banner

“ዝክረ ዓድዋ ኢትዮጵያዊነት” የካቲት 20 ብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል

#FastMereja | “ዝክረ ዓድዋ ኢትዮጵያዊነት” የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር፣ በመጪው አርብ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በታላቁ ብሄራዊ ቲአትር ይካሄዳል፡፡

በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴይንመንት አዘጋጅነት እንደ እስከዛሬዎች ሁሉ ዘንድሮም ለድርጅቱ 1ዐኛውን እንደ ሀገር 13ዐኛውን የአድዋ ድል በዓል “ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት” በተሰኘዉ መርሀ-ግብር ላይ ጥናታዊ ፅሁፍና ዲስኩር በምሁራን የሚቀርብ ሲሆን፤ የግጥም ምሽትና የስታንዳፕ ኮሜዲም እንደተሰናዳ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ፖለቲከኞች በሰላምና አንድነት ዙሪያ አነቃቂ ንግግር፣ እንዲሁም ጀግኖች አርበኞች ሽለላና ፉከራ በባህላዊ ባንድ ታጅበው ያቀርባሉ ተብሏል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ደራሲ ገጣሚ ፀሀፊ ተውኔትና ባለ ቅኔ አያልነህ ሙላቱ፣ አንባሣደር ዲና ሙፍቲ፣ዶ/ርወዳጄነህ ማህረነ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ መምህር ዲያቆን ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ፣ አርቲስት ሙሉአለም ታደስ አርቲስት ሱራፌል ተካ እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ተገልጿል።

የኢትዮጵያውያንና የአፍሪካውያን ብሎም የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ምልክት በሆነው የአድዋ ድል ዋዜማ ላይ በሚካሄደው መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚታደሙም ተገልጿል፡፡

የመግቢያ ዋጋ መደበኛ 3ዐዐ ብር፣ VIP ደግሞ 500 ብር ሲሆን፤ ትኬቱ በቴሌ ብር፣ በጃፋር ቤተ-መፅሐፍት፣ በ2 ሺህ ሐበሻ የባህል ምግብ አዳራሽ ይገኛል።





Leave a Comment