banner

ቴዲ አፍሮ በ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ ያስተላለፈው ወቅታዊ መልዕክት

​#FastMereja I ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፈው መግለጫ፣ በሀገሪቱ እየታየ ያለው የሰላም እጥረት እና የማንነት ጥቃት እጅግ እንደሚያሳስበው ገለጸ።

​ድምፃዊው መጀመሪያ የክብር ሰላምታውን በማስቀደም፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን ለታሪካዊውና አንጸባራቂው የዓድዋ ድል በዓል በታላቅ ብሄራዊ ኩራት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል። ይህ በዓል የኢትዮጵያ የነፃነት ተምሳሌት መሆኑን በመጥቀስ ብሄራዊ ኩራቱን ገልጿል።

​በመግለጫው ላይ ቴዲ አፍሮ በሀገሪቱ ካለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል በዝርዝር አንስቷል።
​በልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቅሷል።
​ለዚህ ማህበራዊና ሀገራዊ ቀውስ ዋነኛው መንስኤ ለዓመታት ስር የሰደደው የዘር ፖለቲካ መሆኑን በአፅንኦት ገልጿል። ​በግፍ እየሞቱ ላሉና ትኩረት ለተነፈጉ ንፁሃን ዜጎች “ፍትህ” ይገባቸዋል ሲል ድምጹን አሰምቷል።

​ድምፃዊው ኢትዮጵያውያን ከዘር እና ከሃይማኖት ልዩነት ወጥተው በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል። ​ለጋራ ህልውና ስጋት የሆነውን የዘር ፖለቲካ ስርዓት “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃ ልንለው ይገባል” ሲል አሳስቧል።

​በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት በፀሎት እንዲያስቡም ጠይቋል።

Leave a Comment