#FastMereja I በከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ውስጥ የታሰሩ ግለሰቦችን እንደ ቆሻሻ በሮቶ ውስጥ በመደበቅ እንዲያመልጡ የረዱ የማረሚያ ፖሊስ አባላት በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።
ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቢኒያም ካህሳይ እና ዳንኤል ጎይቶም የተባሉ ታራሚዎች ከጥበቃ ፖሊሶቹ ጋር ቀድመው በመመሳጠር የማምለጫ ዘዴ ቀየሱ። ታራሚዎቹ ቆሻሻ በሚወገድበት “ሮቶ” ውስጥ እንዲደበቁ ከተደረገ በኋላ፣ ተባባሪ ፖሊሶቹ ልክ እንደ ቆሻሻ ከዞን አስወጥተው መጣያ ቦታ እንዲደፉ አድርገዋል። በመጨረሻም ወደ ማረሚያ ቤቱ ቆሻሻ ለመጫን በመጣ ተሸከርካሪ ውስጥ እንደ ቆሻሻ ተጭነው እንዲወጡ ተመቻችቶላቸዋል።
ማረሚያ ቤቱ ባደረገው ፍተሻ ታራሚዎቹ “የውሃ ሽታ” ሆነው ቢቀሩም፣ ተባባሪ የነበሩ 8 ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል። በዚህም መሠረት የገላን ከተማ ፍርድ ቤት የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፦
1ኛ ሳጅን አደም ሽብሩ
2ኛ ም/ሳጅን መንገሻ ደገፋ
3ኛ ረዳት ሳጅን ልጃለም ተሜ የተባሉ ፖሊሶች እያንዳንዳቸው በ1 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ1,000 ብር መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
የማዕከሉ ዳይሬክተር ኮማንደር አላምረው ተረፈ “ማንም ወንጀል ሰርቶ ከሕግ ተጠያቂነት አያመልጥም” ሲሉ ሌሎች አባላት ከእንዲህ ዓይነት ተግባር እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።
