0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ በገበያ ላይ የዋሉ (Batch number 620) መለያ ቁጥር ያላቸው የፋይን (Fine) የታሸጉ የውሃ ምርቶችን ማህበረሰቡ እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ።
በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር የተገኘበት ሲሆን፣ ይህም ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
አምራች ድርጅቱ ከየካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን እንዳያመርትና ወደ ገበያ እንዳያሰራጭ የታገደ ሲሆን፣ በገበያ ላይ ያለውንም በ5 ቀናት ውስጥ እንዲሰበስብ ታዟል።
ድርጅቱ ምርቱን ሲያመርት የመልካም አመራረት ሥርዓትን ያልተከተለ መሆኑን ባለስልጣኑ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ማህበረሰቡ ይህንን መለያ ቁጥር (Batch 620) ያለውን ውሃ ከመጠቀም እንዲቆጠብና በገበያ ላይ ሲያገኝም በነጻ የጥቆማ መስመር 8864 ላይ ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።
ድርጅቱ የችግሩን መነሻ ለይቶ አሳውቆና ማስተካከያ ማድረጉ ተረጋግጦ በጽሁፍ ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ ምርቱን ማከፋፈል እንደማይችል ተገልጿል።
