banner

“ለምን” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ተመረቀ

#FastMereja I በደራሲ አዱኛ ሂርጳ የተጻፈውና ለሁለት ዓመታት ዝግጅት የተደረገበት “ለምን” የተሰኘው አዲስ የልብ-ወለድ መጽሐፍ፣ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በወዳጅነት ፓርክ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን፣ የቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር አቶ ሺፈራው ወልደሚካኤል፣ ዶክተር ምህረት ደበበ እና የጠብታ አምቡላንስ መሥራች አቶ ክብረት አበበ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

መጽሐፉ በ400 ገጾችና በ53 ምዕራፎች የተቀነበበ ሲሆን፣ “ለምን?” ብሎ በመጠየቅ ለውጥ ለማምጣት የሚጋደልን ግለሰብ ታሪክ፣ የኢትዮጵያን እግር ኳስና ማህበራዊ ጉዳዮችን አጣምሮ የያዘ ነው።

በቢንያም አቡራ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅኝት ቀርቧል።

መጽሐፉን በአገር ውስጥ በጃፋር መጽሐፍት መደብር፣ በውጭ ሀገር በአማዞን (Amazon) ይገኛል።





Leave a Comment