banner

ስፔን አምባሳደሯን ከእስራኤል አስወጣች

#FastMereja I ​የስፔን መንግስት በእስራኤል የሚገኙትን አምባሳደሯን ለማስወጣት መወሰኑን በይፋዊ መግለጫ አስታውቋል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ማክሰኞ March 10, 2026 በተደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው።

​ስፔን እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ጦርነት “የዘር ማጥፋት” በማለት በመቃወም ከአውሮፓ ህብረት ግንባር ቀደም ነቀፌታ አቅራቢ ሆና ቆይታለች።

​አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን አዲስ ጦርነት ስፔን አጥብቃ ትቃወማለች።
​
ስፔን ቀደም ሲል በእስራኤል ላይ የጦር መሳሪያ ሽያጭን በቋሚነት የሚከለክል ህግ ማፅደቋ ይታወሳል።
​
​የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሰነዘሩት ጥቃት “ምክንያት አልባ” ነው በማለት ኮንነዋል። መንግስታቸውም ለጦርነት “አይ” የሚል ግልጽ አቋም እንዳለው ገልጸዋል።

​በአምባሳደር አና ማሪያ ሳሎሞን ፔሬዝ ምትክ፣ በቴል አቪቭ የሚገኘው የስፔን ኤምባሲ በጊዜያዊ መላክተኛ እንደሚመራ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ሲል አልጀዚራ ነው ያስነበበው።

Leave a Comment