0
#FastMereja I የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ።
ዋና ዳይሬክተሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ አክለውም፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግና ከአደጋው በኋላ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች ምላሽ ለመስጠት የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
