0
#FastMereja I የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን፣ በጋጮ ባባ ወረዳ፣ ላካ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን አወጀ።
መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰው በዚህ አሰቃቂ አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ ከ125 በላይ ሰዎች ለጉዳት የተዳረጉ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ የ80 ወገኖች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። የተቀሩት ደግሞ በከባድ ፍለጋ ላይ ይገኛሉ።
ምክር ቤቱ ከአዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ ከነገ መጋቢት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን እንዲሆን ወስኗል።
በእነዚህ የሐዘን ቀናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተወስኗል።
