banner

በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የተሳሳቱ እና የሃሰት ቪዲዮዎችን ያሰራጩ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

#FastMereja I ​የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ የዲጂታል መድረኮች ላይ ህዝብን የሚያሳስቱ እና የተቀነባበሩ የቪዲዮ ምስሎችን በመልቀቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 10 ተከሳሾች እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

​በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሲሆኑ ​2 ህንዳውያን፣ 1 ፓኪስታናዊ፣ 1 ፊሊፒንሳዊት፣ 1 ግብፃዊ፣ 1 ባንግላዴሻዊ፣ 1 ካሜሩናዊ፣ 1 ኔፓላዊ፣ 1 ቪየትናማዊ እና 1 ኢራናዊ ናቸው።

​ባለስልጣናት እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹ ያሰራጯቸው ቪዲዮዎች፦ ​እውነተኛ እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተቀነባበሩ ምስሎችን በመጠቀም በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ የቦምብ ፍንዳታዎች፣ ጥቃቶች እና የደህንነት ስጋቶች እንዳሉ የሚያሳዩ የሃሰት መረጃዎች ናቸው።

​ምርመራው እንደሚያሳየው፣ የቪዲዮዎቹ ዋና ዓላማ ህዝቡን ማሳሳት እና ፍርሃትን መርጨት ነው።

​ተከሳሾቹ በአፋጣኝ ለፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጓል።
​እንዲህ ያሉ የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር መሆኑን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

​በህጉ መሰረት ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ ግለሰቦች ቢያንስ የአንድ ዓመት እስራት እና ከ 100,000 ድርሃም (AED) ጀምሮ የሚቀጣ የገንዘብ መቀጮ ይጠብቃቸዋል።

Leave a Comment