0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለጤና ጎጅ የሆነ አደገኛ ኬሚካል ወደ ወንዝ በመልቀቁ ሁለት ሚሊዮን ብር መቅጣቱን አስታወቀ።
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታ ተግባረዕድ አካባቢ ብክለቱ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች አደገኛና ለጤና ጎጂ ኬሚካል መኖሩ በላብራቶሪ ናሙና ተወስዶ የተረጋገጠ በመሆኑና ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ጥፋት የተቀጣ በመሆኑ በሪከርድ ሁለት ሚሊዮን ቅጣት እንደተጣለበት ነው ባለስልጣኑ የገለፀው።
ቅጣቱ የተወሰነው በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት መሆኑን ባለስልጣኑ ጠቅሷል።
