banner

የካቻ ዲጂታል ፋይናንስ የባንክ ሒሳቦች እግድ ተነሳ፤ ተቋሙ ወደ መደበኛ ሥራው ተመለሰ

​#FastMereja I የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ አክሲዮን ማኅበር የባንክ ሒሳቦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ውሳኔው ኩባንያው ሁሉንም የሥራ ማስኬጃ ሒሳቦቹን በመጠቀም መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል የሚያስችል ነው።
​
​የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሦስት ዳኞች ስብስብ በመዝገብ ቁጥር 364130 ባስተላለፈው ውሳኔ፣ ካቻ ዲጂታል ፋይናንስ ካሉት በርካታ የባንክ ሒሳቦች መካከል ከውርርድ ተግባር ጋር በተያያዘ ምርመራ እየተደረገበት ያለው 3,110,249.74 (ሦስት ሚሊዮን አንድ መቶ አሥር ሺህ ሁለት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከ74 ሳንቲም) ብቻ ተለይቶ ታግዶ እንዲቆይ አዝዟል። ይህ የተጠቀሰው ገንዘብ እየተካሄደ ያለው ምርመራ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ የሚቆይ ቢሆንም፣ የተቀሩት የኩባንያው እንቅስቃሴዎች ግን እንዲቀጥሉ ተፈርዷል።

​ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ላይ ምርመራው በሚቀጥልበት ወቅት የኩባንያውን ህልውና እና የንግድ ሥራ ለማስቀጠል ያልተገደበ የሒሳብ እንቅስቃሴ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቷል። ቀደም ሲል ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ተጥሎ የነበረው ጠቅላላ እግድ የኩባንያውን የዕለት ተዕለት ሥራ በእጅጉ ሲያስተጓጉል መቆየቱ ይታወሳል።

​መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም

Leave a Comment