banner

አማራ ባንክና ቪዛ በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያዎችን ለማዘመን ተስማሙ

​#FastMereja I መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም.

​አማራ ባንክ በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለማፋጠንና ዘመናዊ ለማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዘርፉ መሪ ከሆነው ቪዛ (Visa) ጋር ስትራቴጂካዊ የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ። ይህ ስምምነት አማራ ባንክ የቪዛን ዓለም አቀፍ አውታረ መረብና የቴክኖሎጂ ልምድ በመጠቀም የካርድ አቅርቦት አቅሙን እንዲያሰፋና የክፍያ መሠረተ ልማቱን እንዲያሻሽል ያስችለዋል። ባንኩ በስምምነቱ መሠረት የቪዛ ቅድመ ክፍያ (Prepaid) እና የዴቢት ካርድ አማራጮችን ለደንበኞቹ ማቅረብ ይጀምራል።

​አማራ ባንክ የቪዛ ክላሲክ፣ ጎልድና ፕላቲኒየም የቅድመ ክፍያ ካርዶችን እንዲሁም የዴቢት ክላሲክ አማራጮችን ለደንበኞች ያቀርባል።

​
አጋርነቱ ማጭበርበርንና የአደጋ ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ የክትትል መሣሪያዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ያካትታል።
ደንበኞች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን አስተማማኝ የክፍያ መሣሪያዎች እንዲያገኙ ዕድል ይፈጥራል።

​ስምምነቱ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳና የጥሬ ገንዘብ አልባ ማህበረሰብ ምስረታን ለመደገፍ ያለመ ነው።
​
​የአማራ ባንክ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ እሸቴ የማታ፣ ስምምነቱ ባንኩ በዲጂታል ክፍያ ዘርፍ ቀዳሚ ለመሆን ለሚያደርገው ጉዞ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው፣ ትብብሩ ለኢትዮጵያውያን ምቹ የክፍያ አማራጮችን ከማቅረብ ባለፈ የባንኩን የፈጠራ አቅም እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል።

#ቢዝነስ መረጃ


Leave a Comment