0
#FastMereja I መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም.
የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን (ቀይ ባህር ግመሎች) ከ18 ዓመታት ረጅም የዝምታ ጉዞ በኋላ፣ ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚያደርገውን የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ረቡዕ ከኤስዋቲኒ ጋር በሞሮኮ መክነስ ከተማ ያካሂዳል። በአሰልጣኝ ሄሻም ያካን የሚመራው የኤርትራ ስብስብ፣ በውጭ ሀገራት የሚጫወቱ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን በማካተት ለዚህ ታሪካዊ ምለሽ ዝግጅቱን አጠናቋል።
የዛሬው ተጋጣሚ ኤስዋቲኒ ጠንካራ የመከላከል መዋቅር ቢኖራትም፣ ባለፉት አራት ጨዋታዎቿ ማስቆጠር የቻለችው ሁለት ጎሎችን ብቻ መሆኑ ለኤርትራ መልካም አጋጣሚ ተደርጎ ተወስዷል። ይሁን እንጂ ኤርትራ ለረጅም ጊዜ ከዓለም አቀፍ ውድድሮች ርቃ መቆየቷ የተጫዋቾችን ቅንጅት ሊፈታተነው እንደሚችል ይገመታል። ጨዋታው በሁለቱም ወገኖች ጥንቃቄ የታከለበትና ጥቂት ጎሎች የሚቆጠሩበት እንደሚሆን የቴክኒክ ባለሙያዎች እየተነበዩ ይገኛሉ።
የኤርትራ ስብስብ በሼፊልድ ዩናይትድ የሚጫወተው ሲያም እዮብ አብርሃ እና በግብፅ ሊግ ውጤታማ የሆነው አሊ ሱሌይማንን ጨምሮ 24 ተጫዋቾችን ይዟል።
