banner

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የተላለፈ አስቸኳይ ውሳኔ

#FastMereja የኢፌዴሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በ52 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የወሰደውን የዕውቅና ስረዛ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲደረግ አዘዘ። ባለስልጣኑ ውሳኔውን ያስተላለፈው ተቋማቱ በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን የጥራት ማሻሻያ መመሪያ ባለማክበራቸውና በህገ-ወጥ መንገድ ትምህርት ሲሰጡ በመገኘታቸው መሆኑን ገልጿል።

የባለስልጣኑ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እነዚህ ተቋማት ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፣ የተጣለባቸውን ግዴታ ሳይወጡ ቀርተዋል። በተለይም በብሔራዊ የከፍተኛ ትምህርት ምዝገባ ሥርዓት (Higher Education Management Information System) ውስጥ ካለመካተታቸውም በላይ፣ በአካል ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበላቸው ህጋዊ ሰውነታቸው እንዲቋረጥ ተወስኗል።

ባለስልጣኑ ለክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ለከተማ አስተዳደሮች፣ ለፍትህ አካላት እና ለፖሊስ ኮሚሽኖች በላከው ደብዳቤ፣ እነዚህ ተቋማት በአፋጣኝ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እና አስፈላጊው የህግ እርምጃ እንዲወሰድባቸው አሳስቧል። ይህ ውሳኔ የተማሪዎችን መብት ለማስጠበቅና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የታለመ መሆኑም ተገልጿል።

በዝርዝሩ ከተካተቱት 52 ተቋማት መካከል

1 አቢሲኒያ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
2 አፍራን ቀሎ ኮሌጅ
3 አገው ምድር ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
4 አዲስ ፋና ኮሌጅ
5 ቢኤ ኮሌጅ
6 ኡቡንቱ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
7 ፈጣም ኮሌጅ
8 ግሪን የምርምርና የልማት ተቋም
9 ሴንቸሪ ኮሌጅ
10 ኮቻ ኪድማስ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
11 ካንድል ላይት የርቀት ትምህርት ኮሌጅ
12 ቀይ ባህር ኮሌጅ
13 ማራኪ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ
14 ኒው ዲፕሎማት ኮሌጅ
15 ፒቢቲ አፍሪካ ኮሌጅ
16 ኳሊቲ ስኮላር ኮሌጅ
17 ራዲካል ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
18 ውቅያኖስ ኮሌጅ
19 የኔታ ኢንጅነሪንግ ኮሌ
20 ቪዥነሪስ የድህረ ምረቃ ኮሌጅ
21 ባቱ ግሎባል ኮሌጅ
22 ባህረ ጥበብ ጤናና ቢዝነስ ኮሌጅ
23 ማይክሮ ቢዝነስ ኮሌጅ
24 ማያ ኮሌጅ
25 ትሪፕል ኮሌጅ
26 ቤታሎጎ ኮሌጅ
27 ቤካ ኮሌጅ
28 ቀስተ ደመና ኮሌጅ
29 ብራይት ቪዥን ኮሌጅ
30 ኤ.አር.ቲ ሜዲካል ኮሌጅ
31 ኢሊያስ ኮሌጅ
32 ሳይፕሮ ኮሌጅ
33 ዳይናሚክ ኮሌጅ
34 ግራንድ ማርክ ኮሌጅ
35 ዱርማን ኮሌጅ
36 ህብረት ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
37 አይቤክስ ሆቴልና ቱሪዝም ኮሌጅ
38 አይ ኪው ኮሌጅ
39 ገራይ ኮሌጅ
40 ጋላክሲ ቢዝነስና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
41 ቪዥን ላንድ ኮሌጅ
42 መራ ሄመንገድ ኮሌጅ
43 ዩናይትድ ኦሮሚያ ኮሌጅ
44 ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኮሌጅ
45 ሲምለስ የርቀት ትምህርት ኮሌጅ
46 ዛክቦን ኮሌጅ
47 ኤም ኤስ ኤል ጂ ኮሊጅ
48 ስሪሳይ ኮሌጅ
49 ፋም ኮሌጅ
50 ስማርት ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
51 ሊድስታር ኮሌጅ ኦፍ ቢዝነስና ሊደርሺፕ
52 ዳሎል የቲክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ

Leave a Comment