banner

10ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደ ርዕይና 2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርት ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ

#FastMereja I 10ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደ ርዕይና ጉባኤ እንዲሁም 2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ዛሬ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር (AICC) በይፋ ተከፍቷል። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) እና በፕራና ኢቨንትስ ትብብር የተዘጋጀው ይህ ታላቅ ኹነት ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ ከ8 ሀገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ አውደ ርዕይ በጤናው ዘርፍ ያለውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት ለመሙላትና የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል። የዘንድሮው መርሃ ግብር ከኤግዚቢሽኑ ባሻገር ከ40 በላይ የሙያ ማጎልበቻ (CPD) ስልጠናዎችን እና 3ኛው የዲጂታል ኸልዝ ሃካቶንን ያካተተ በመሆኑ ለባለሙያዎች ልዩ የዕውቀት መጋሪያ መድረክ ፈጥሯል።

ኢትዮጵያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ቱርክ፣ ባንግላዴሽ፣ ዩኤኢ እና አሜሪካ ሀገራት ተሳታፊ ሲሆኑ ከ20 በላይ የሙያ ማህበራት ጋር በመተባበር የሚከናወኑ ሳይንሳዊ ፎረሞች እና የንግድ ትስስር መድረኮች ተዘጋጅተዋል።

መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

#ኹነት





Leave a Comment