0
#FastMereja I ኢራን የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት ተገቢና የሚደነቅ መሆኑን ገለጸች።
በኢትዮጵያ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አሊ አክባር ራዛኒ ከአሐዱ ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድና በድርድር የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው እንቅስቃሴ ለቀጣናው መረጋጋትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል። አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የኢኮኖሚ አቅምና የሕዝብ ብዛት የባሕር በር መዳረሻ እንዲኖረው የግድ የሚል መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
መንግሥት ጥያቄውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት የሚያሳየው ቁርጠኝነት የሚመሰገን መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፣ ሂደቱ በድርድርና ለሀገሪቱ ዘላቂ ዋስትና በሚሰጥ መልኩ መከናወኑ ለቀጣናዊ ትስስር የላቀ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል። ይህ የኢራን ድጋፍ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ለማጠናከር ለምታደርገው ጥረት ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ ግብዓት እንደሚሆን ይጠበቃል።
መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
