banner

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ክስ መሰረተ

​#FastMereja I የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል፣ በወንጌላውያን አማኞች መንፈሳዊ ገጽታ ላይ ጥላሸት ቀብተዋል ያላቸውን ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ ክስ መመስረቱን አስታወቀ። ካውንስሉ ክሱን የመሰረተው ወ/ሮ ገነት ንጋቱ እና አቶ አንተነህ ተኸርቁ ባደረጉትና በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ቃለ መጠይቅ ላይ በመነሳት እንደሆነ ገልጿል።

​ካውንስሉ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በሁለቱ ግለሰቦች መካከል በተደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ለአማኙ ማህበረሰብ ካላቸው ጥላቻ በመነሳት የእምነቱን ተከታዮች መንፈሳዊ ገጽታ የሚያበላሽ ንግግር ተሰራጭቷል። በተለይም የተጠቀሰው ጉዳይ እውነት ከሆነ የአገልጋዩን ማንነት በስም መጥቀስ ሲገባ፣ ይህ ሳይደረግ በደፈናው የቀረበው ክስ ሆን ተብሎ የእምነቱን ገጽታ ለማበላሸት የታለመ ነው ብሏል።

​በመሆኑም ተገቢው የህግ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ክስ የመሰረተ ሲሆን፣ በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ መድረኮችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባልተከተለ መንገድ የወንጌል አማኞችን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ካውንስሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።ከ

Leave a Comment