0
#FastMereja I እስራኤል በሊባኖስ ላይ በፈጸመችው የቅርብ ጊዜ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን የሊባኖስ የጤና ሚኒስትር ራካን ናሰረዲን ለአልጀዚራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ። ጥቃቱ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ የተፈጸመና እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ መሆኑ ተገልጿል።
እንደ ጤና ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በሊባኖስ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ድንገተኛና ተከታታይ ጥቃት ፈጽመዋል። ሚኒስትር ራካን ናሰረዲን “በመቶዎች የሚቆጠሩ” ሲሉ የገለጹት የሟቾችና የቁስለኞች ቁጥር አሁንም በየጊዜው እየጨመረ መሆኑንና የጤና ተቋማት በተጎጂዎች ብዛት መጨናነቃቸውን አመልክተዋል።
