0
#FastMereja I በዎላይታ ዞን በዴሳ ከተማ ዛሬ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። ከአይን እማኞች በተገኘው መረጃ መሰረት፣ ከዎላይታ ሶዶ አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረ አንድ ተሳቢ የጭነት መኪና በፍሬን ብልሽት ምክንያት ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ሶስት ቤቶችን ጥሶ ገብቷል።
እስካሁን ባለው መረጃ የሟቾች ቁጥር በውል ባይታወቅም፣ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። የአካባቢው ነዋሪዎች እና የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍርስራሹ ውስጥ የተከለሉ ሰዎችን ለማውጣት ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።
