0
#FastMereja I የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን የውድድር መርሃ-ግብር ላይ ተመዝግበው ሳይገኙ በቀሩ አትሌቶች ላይ ጥብቅ የዲስፕሊን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ። ፌዴሬሽኑ አትሌቶቹ በከሰዓቱ ውድድር ላይ እንዲገኙ የመጨረሻ ጥሪ አስተላልፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቀድመው ምዝገባ ቢያካሂዱም፣ በጠዋቱ መርሃ-ግብር ላይ ያልተገኙ መኖራቸው ተገልጿል። ይህ መቅረት በውድድሩ ሂደት ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን የጠቆመው ፌዴሬሽኑ፣ ድርጊቱ የስፖርታዊ ጨዋነት መመሪያን የሚጥስ መሆኑን አሳስቧል።
