banner

“የሰዎች ኮሜት ቦኒ ራሷን እንድታጠፋ አድርጓታል” ወዳጆቿ

#FastMereja I በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን በማፍራት የምትታወቀው ወጣት የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦኒ (Boni) ባልተጠበቀ ሁኔታ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተነገረ። ወጣቷ ከህልፈቷ አስቀድሞ በማህበራዊ ገጾቿ ላይ የስንብት የሚመስል መልዕክት ማጋራቷ በደጋፊዎቿ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል።

ቦኒ በቲክቶክ እና በፌስቡክ በርካታ ተከታይ ያላት ሲሆን በይዘት ፈጣሪነቷ ስኬታማ ከሆኑ ወጣቶች ተርታ ትመደባለች። ይሁን እንጂ ህይወቷ ከማለፉ ጥቂት ቀደም ብሎ ባስተላለፈችው መልዕክት፣ በህይወት ጉዞዋ የገጠሟትን ተግዳሮቶች በማንሳት “ለሁላችሁም ይቅርታ አድርጌያለሁ፣ እናንተም ይቅር በሉኝ” የሚል ልብ የሚነካ ቃል አስፍራለች።

ይህ አሳዛኝ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶች እና የቃላት ጥቃቶች በሰዎች ስነ-ልቦና ላይ የሚያሳድሩትን ጥልቅ ጠባሳ ልጅቷን እንደጎዳት ወዳጆቿ ይናገራሉ። በርካታ ተከታዮቿም የህልፈቷን ዜና ተከትሎ የሀዘን መግለጫቸውን እያስተላለፉ ይገኛሉ።

Leave a Comment