0
#FastMereja I በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ቶጫ ወረዳ ውስጥ፣ በመኝታ ላይ በነበረ የገዛ ባለቤቷ ላይ የፈላ ውሃ በመድፋት ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰችው ፋናዬ ኦሎሎ የተባለች ግለሰብ፣ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ተወሰነባት።
በወረዳው ገዳ ሜላ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ተከሳሽ ፋናዬ ኦሎሎ፣ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ላይ ነበር ጥቃቱን የፈጸመችው። እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ፣ ተከሳሿ በብረት ድስት ያፈላችውን ውሃ፣ ተበዳይ ባለቤቷ በመኝታው ላይ ተኝቶ ባለበት ወቅት በላዩ ላይ በመድፋት ከአንገቱ እስከ ጀርባው ድረስ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስበት አድርጋለች።
የቶጫ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ባደረገው ማጣራትና የመሰረተው ክስ በወረዳው ፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል። ፍርድ ቤቱ የቀረቡትን የሰውና የህክምና ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ፣ ተከሳሿ በፈጸመችው ድርጊት ጥፋተኛ መሆኗን አረጋግጧል።
በዚህም መሰረት የቶጫ ወረዳ ፍርድ ቤት በዋለው የወንጀል ችሎት፣ ድርጊቱ “ጭካኔ የተሞላበት” መሆኑን በመጥቀስ፣ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል።
