banner

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

​#FastMereja I ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በታዳሽ ኃይል እና በዲጂታላይዜሽን ዘርፎች ላይ የሚያተኩር የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱ የተፈረመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በሁለትዮሽ እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ከመከሩ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

​ይህ ስምምነት በዋናነት የተቀናጀና ዘላቂ ኃይልን ለማልማት እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር የሚውል ነው። ከገንዘብ ብድር ስምምነቱ በተጨማሪ ሁለቱ ሀገራት የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ አድርገዋል።

​ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት፣ ከፕሬዝዳንት ማክሮን ጋር ያደረጉት ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ቁልፍ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመለወጥ ያለመ ነው። በውይይቱ ወቅትም በታዳሽ ኃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።

Leave a Comment