banner

በደብረ ማርቆስ መስመር በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የተጎዱ ወገኖች ቤተሰብ በአስቸኳይ እንዲመጣላቸው ተጠየቀ

#FastMereja I ከደብረ ኤልያስ ወደ ደብረ ማርቆስ 24 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ በነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እና ከደብረ ማርቆስ ወደ ባሕር ዳር መስመር ይጓዝ በነበረ የጭነት መኪና መካከል በደረሰ ግጭት በሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ። አደጋው “ሰንተራ ሜዳ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ተጎጂዎቹ በደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

በአደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖች መካከል አብዛኞቹ በቅርብ የሚያውቃቸው ቤተሰብም ሆነ ዘመድ አብሯቸው ባለመኖሩ፣ ሆስፒታሉ አስፈላጊውን የህክምና ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ በሂደት ላይ መቸገሩ ታውቋል። በመሆኑም ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የሚያውቁ ቤተሰቦች ወይም የቅርብ ወዳጆች በአስቸኳይ ወደ ደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመምጣት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

Leave a Comment