banner

በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ የትግራይ ዲያስፖራ አባላት በትግራይ ላይ “አንዣብቧል” ያሉትን የጦርነት ስጋት በመቃወም ሰልፍ አደረጉ

በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ የትግራይ ዲያስፖራ አባላት በትግራይ ላይ “አንዣብቧል” ያሉትን የጦርነት ስጋት በመቃወም ሰልፍ አደረጉ

#FastMereja I በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ የትግራይ ዲያስፖራ አባላት በትግራይ ክልል ላይ አንዣብቧል ያሉትን የጦርነት ደመና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀውና እንዲያስቆመው በመጠየቅ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (State Department) ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተሰምቷል።

የአካባቢው ተወካይ አቶ ሚዛን ገብረስላሴ ለድምጺ ወያኔ በሰጡት መረጃ መሰረት፤ በክልሉ ወደ መደበኛ ስራው የተመለሰው መንግስትና ምክር ቤት የህዝቡን ችግሮች በፍጥነት መፍታት እንዳለባቸውና ህዝቡም ከመንግስት ጎን ሊቆም እንደሚገባ አመልክተዋል።


Leave a Comment