banner

ማርቨለስ ሪል እስቴት ያስገነባቸውን ባለ 3 መኝታ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ለደንበኞቹ አስረከበ

#FastMereja I ማርቨለስ ሪል እስቴት በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ያስገነባቸውን 48 ባለ ሶስት መኝታ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በታላቅ ስነ-ስርዓት ለደንበኞቹ አስረክቧል። በቤት ማስተላለፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል።

ኩባንያው ቤቶቹን ከመሸጥ ባለፈ የንብረት አስተዳደር አገልግሎትን በራሱ ባለሙያዎች እንደሚያከናውንና ይህም የቤቶቹን ዘመናዊ ጥገና እና ጥበቃ አስተማማኝ በማድረግ የደንበኞችን የሀብት ዋጋ ለረጅም ጊዜ ጠብቆ ለማቆየት እንደሚያስችል ተብራርቷል።

የተረከቡት አፓርታማዎች የሀገር ውስጥ ባህልን መሰረት ያደረጉ፣ ከማህበራዊ እሴቶች ጋር የተጣጣሙ እና እንደ ደንበኞች ምርጫ በከፊል (Semi-finished) ወይም ሙሉ በሙሉ (Fully-finished) ተጠናቀው የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል።

ፕሮጀክቶቹ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ እንዲያርፉ የተደረገበት ምክንያት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ለመኖሪያ ምቹ፣ ወደ ዋና ዋና የከተማዋ ክፍሎች ለመጓዝ በርካታ አማራጭ መንገዶች ያሉት እና በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየለማ ያለ አካባቢ በመሆኑ ስትራቴጂያዊ ምርጫ ተደርጎ እንደሆነም ተነግሯል።

ማርቨለስ ሪል እስቴት ከዚህ ቀደም ከ40 በላይ ባለ 3 መኝታ ቤቶችን ያስረከበ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም በዚህ በኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ተጨማሪ የ4 ሳይቶችን ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እያከናወነ እንደሚገኝ ተነግሯል።





Leave a Comment