banner

ታላቁ የሐዋሳ የሙዚቃ ኮንሰርት በሰቨን ላውንጅ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

​#FastMereja I በሐዋሳ ከተማ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረውና ታዋቂ ድምፃውያንን በአንድ መድረክ ያገናኘው ልዩ የሙዚቃ ድግስ ትናንት ምሽት በሰቨን ላውንጅ (Seven lounge) በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ።

​በደቡብ ኢትዮጵያ እምብርት በሆነችው በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ በተካሄደው በዚህ ታላቅ ምሽት ላይ ተወዳጆቹ ድምፃውያን ወንድሙ ጂራ፣ ሐይሌ ሩት፣ ቶኪቸው እና ናሆም መኩሪያ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በቅብብሎሽ አቅርበዋል። አርቲስቶቹ መድረኩን በተራ በተራ በተቆጣጠሩበት ወቅት ከተመልካቹ የተሰጣቸው ምላሽና የታየው አጠቃላይ ስሜት ከፍተኛ እንደነበር ለመታዘብ ተችሏል።

​የኮንሰርቱ አስተባባሪዎች ለፋስት መረጃ እንደገለጹት፣ ዝግጅቱ የታለመለት የሙዚቃ አፍቃሪዎችን የማዝናናትና ልዩ ትዝታ የመጣል ግብ ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል። በሰቨን ላውንጅ የተገኘው ታዳሚም አርቲስቶቹን በልዩ ሁኔታ ያበረታታ ሲሆን፣ የምሽቱ ድባብ በከተማዋ የኪነ-ጥበብ እንቅስቃሴ ላይ አዲስ መነቃቃትን የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።





Leave a Comment