banner

ህወሓት በክልሉ ያሉ ህዝቦች በረሃብ እና በሽታ እየተሰቃዩ ነው አለ!

​#FastMereja I ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ፣ የፌደራል መንግሥት ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት በትግራይ ሠራዊት አባላት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ገለጸ። ድርጅቱ በትግራይና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው ውጥረት አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል።

​በመግለጫው መሠረት፣ የትግራይ ክልል 40 በመቶ መሬት አሁንም በሌሎች ኃይሎች እጅ እንደሚገኝና ከተፈናቀሉበት መሬት ውጭ ያሉ ወገኖች በረሃብና በበሽታ እየተሰቃዩ መሆኑ ተገልጿል።

የፌደራል መንግሥት የትግራይን ሰላም ለማናጋት በዓፋርና በጸለምቲ በኩል አዲስ የደም ማፋሰስ ጦርነት ለመክፈትም ከጫፍ እስከ ጫፍ መሣሪያና ሠራዊት እያስገባ መሆኑን ህወሓት በመግለጫው አስፍሯል።

​ህወሓት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ድርጅቱ ራሱን ፈትሾ ያደረገው መዋቅራዊ ጥንካሬ እና የትግራይ ሠራዊት (TDF) ክልሉን ለመከላከል በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኙ ገልጾ፤ በትግራይ ውስጥና ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ ተጋሩ ሙሉ አቅማቸውን አስተባብረው ለህልውና እና ለሉዓላዊነት እንዲታገሉ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህ ዙሪያ ከፌደራል መንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

Leave a Comment