0
#Fastmereja I በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ገበያ ውስጥ ሸማቶች የተለያዩ ብራንዶችን በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ለማስቻል «ቴክ ኢዚ» (TekEasy) የተሰኘው የኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ማዕከል የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በይፋ አስመርቋል።
ማዕከሉ እንደ ቴክኖ፣ አፕል፣ ሚዲያ እና ኢንፊኒክስ ያሉ ታዋቂ ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።
ኩባንያው በአዲስ አበባ የጀመረውን ይህንን የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት በቀጣይ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች የማስፋፋት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።
ይህ ማዕከል ከተለመደው የሽያጭ አሰራር በተለየ መልኩ ከሽያጭ በኋላ በሚሰጥ አገልግሎት የያዘ ሲሆን ዕቃዎችን ደንበኞች እስከሚፈልጉበት ቦታ ድረስ የሚያደርስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሁም የቴክኒክ ብልሽቶች በሚያጋጥሙበት ወቅትም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የጥገና ማዕከልና የባለሙያ ቡድን የተደራጀ ስለመሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ አዲስ ማዕከል በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዲጂታል ኑሮ ዘይቤ በማገዝና ለሸማቾች አስተማማኝ አማራጭ በመሆን ረገድ የራሱን አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።




