banner

እናትየው ባረፉበት ዕለት ፈተናውን የተፈተነው የ8ኛው ክፍል ተማሪ

#FastMereja | ታዳጊ ካሊድ ቃሲም ይባላል፤ የየካ ጣፎ ነዋሪ ሲሆን Muuxxannicha ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነው። በትናንትናው እለት ረፋድ ላይ እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ፣ ታዳጊው ካሊድ “ምንም ዓይነት ችግር ቢገጥምህ ትምህርትህን እንዳታቋርጥ” የሚለውን የእናቱን የመጨረሻ ኑዛዜ በማስታወስ፣ የሁለት የጠዋት ፈተናዎችን ለመፈተን ወደ ማዕከሉ አምርቷል። በምሳ ሰዓት እረፍት ወደ ቤቱ በመመለስ የእናቱን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ያከናወነው ታዳጊው፣ ከሰዓት በኋላም ወደ ፈተና ጣቢያው በመመለስ ቀሪውን ፈተና በአግባቡ አጠናቋል።

የታዳጊው እናት ከዚህ ዓለም በሞት ከመለያየታቸው በፊት ከካሊድ በተጨማሪ ሁለት ትናንሽ ህፃናትን ጥለው ማለፋቸው ታውቋል። በመሆኑም ካሊድ በአሁኑ ወቅት ከዕድሜው በላይ የሆነውን የቤተሰብ ኃላፊነት ለመሸከም ተገዷል። አባቱ በጅጅጋ ከተማ ሌላ ትዳር መሥርተው እንደሚኖሩ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ታዳጊውንና ወንድሞቹን በዘላቂነት ለመርዳት የባንክ አካውንት የመክፈት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል። አስፈላጊው መረጃ እንደተጠናቀቀ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

Leave a Comment