banner

ደራሲ ታቲያና ሁለት የሕጻናት መጽሕፍትን አስመረቀች

​#FastMereja I ​የሕጻናት መጻሕፍት ደራሲዋ ታቲያና ክፍሌ ዛሬ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍትን አስመርቃለች። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው “ፊሽታ” የተሰኘው መጽሐፍ አራተኛው ክፍል ሲሆን፣ ​ሁለተኛው መጽሐፍ “የንግሥተ ሳባ” የታሪክ መጽሐፍ ሲሆን፣ ከተለያዩ መጻሕፍት በማንበብ፣ ከሁሉም ታሪኮች በማቀናጀት ለህጻናት በሚመች መልኩ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

​ደራሲ ታቲያና ባደረገችው ንግግር “ልጆቻችንን ዓለም ከሚያሳድገው በየቤተ እምነቶቻችን አሳድገን መልካም ትውልድ፣ ነገም አገር የሚረከብ ትውልድ እንድናፈራ” ብላለች።

​መጻሕፍቱ በየቤተ መጻሕፍቱ ለማሰራጨት እየተሞከረ ሲሆን፣ ለጊዜው በአምስት መጻሕፍት መደብር እና በአማዞን ድረ-ገጽም የሚገኙ ይሆናል። መጻሕፍቱ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅተዋል።

​ደራሲ ታቲያና፣ ፊሽታ የተሰኘው መጽሐፍ ከሶስት አመት በላይ ጥረት የተደረገበት እና ለተለያዩ የእድሜ ክልሎች ተደራሽ እንዲሆን የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጻለች።





Leave a Comment