banner

በዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የተሰናዱ ሁለት የሳይንስና የወደፊት ራዕይ መጻሕፍት ተመረቁ!

#Fastmereja:- በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በሰው ልጅ ቀጣይ ስልጣኔ ላይ የሚያተኩሩ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍት በዛሬዉ እለት በልዩ ስነ-ስርዓት ተመረቁ።

የቴክኖሎጂ ባለሙያውና ተመራማሪው ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ያዘጋጇቸዉ «Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization>> እና «Introduction to Astronautics: A Beginner’s Guide» የተሰኙት መጻሕፍት፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካዳሚክ ማህበረሰብ፣ ዲፕሎማቶችና የቴክኖሎጂ ዘርፍ አጋሮች በተገኙበት ነው ለንባብ የበቁት።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ደራሲው ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ፣ መጻሕፍቱ የተዘጋጁት መረጃ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን አገር በቀል እውቀትን በማሳደግ የወደፊቱን ትውልድ ለታላቅ ስኬት ለማነሳሳት መሆኑን ገልጸዋል።

“ሀገራት የሚለወጡትና ከፍ የሚሉት በእውቀት፣ በፈጠራ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ራዕይ ብቻ ነው” ያሉት ደራሲው፣ ሁለቱ መጽሐፍት በይዘታቸው የተለያዩ ቢመስሉም የሚያስተላልፉት መልዕክት ግን በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ የሚቀመር መሆኑን አስገንዝበዋል።

የመጀመሪያው መጽሐፍ-«Architecting the Future» -አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ ሮቦቲክስ፣ ኳንተም ኮምፒውቲንግ፣ ባዮቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ የሰው ልጅን ህይወት በከፍተኛ ፍጥነት እየቀየሩት ባሉበት በዚህ ወቅት፣ የወደፊቱን ዓለም በሥነ-ምግባር፣ በሰብዓዊ እሴቶችና በፍትሐዊነት እንዴት መምራት እንደሚቻል ስልታዊ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። መጽሐፉ ለመንግሥታት የፖሊሲ አቅጣጫን፣ ለዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ የምርምር ራዕይን ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል «Introduction to Astronautics>> የተሰኘው ሁለተኛው መጽሐፍ የጠፈር ቴክኖሎጂን በቀላል ቋንቋ የሚያስተምር ሲሆን፤ የሮኬት ሳይንስ፣ ሳተላይቶች፣ የጠፈር ህግና ዲፕሎማሲ እንዲሁም የጠፈር ኢኮኖሚ በተግባራዊ መልኩ የቀረቡበት ነው። በተለይም ኢትዮጵያና አጠቃላይ አፍሪካ በአዲሱ የጠፈር ኢኮኖሚ ውስጥ ተገብሮ ተመልካች ሳይሆኑ፣ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው መጽሐፉ በግልጽ እኖደሚያሳይ ተገልጿል።

ዶ/ር ይሹሩን የሁለቱን መጻሕፍት ትስስር ሲያስረዱም፦



Leave a Comment